ስለምን እንሰቃያለን? ስለምን ስቃያችን በዛ? ✍★✍ ሁላችንም እንደምናውቀው ከጊዜ ወደ ጊዜ ከዘመን ዘመን የሰው ልጅ ህይዎት እጅግ እየተሻሻለ ነው። ይሁን እንጅ ይህ የኑሮ ወይም የህይዎት መሻሻል ለሁሉም ሰዎች እኩል ሊሆን አልቻለም። በእርግጥ እኩል እንዲሆን አይጠበቅም። ነገር ግን ተመጣጣኝ ይሆን ዘንድ አስፈላጊ ነው። በአንድም በሌላም ምክንያት ግን ሰዎች የመረረ የስቃይ ሕይዎትን እያሳልፉ ነው። ለምን?ስለምን እንሰቃያለን? እንደኔ ዕይታ ለዚህ ጥያቄ መልሱ “ከተፈጠርንበት ዓላማ ስላፈነገጥን” ይመስለኛል። ነውም። የተፈጠርነውስ ለምንድን ነው?እንግዲህ በሁለቱ ታላላቅ ሀይማኖቶች ማለትም እንደ እስልምና እና ክርስትና አስተምህሮ የሰው ልጅ የተፈተረው ፈጣሪውን በምስጋና ሊያገለግል ነው። በተለይም እንደ ክርስትናው አስተሳሰብ ሰው በፈጣሪው አርአያ ከአራት ባህርያተ ሥጋና ከሦስቱ ባህርያተ ነፍስ ተፈጥሮ አምላኩን እያመሰገነ በኤደን ገነት ይኖር ዘንድ ተፈጠረ። ነገር ግን በመጀመሪያው ሰው አዳም በተለይም ከጎኑ በተገኘችው ሄዋን አዕምሮ ውስጥ ከንቱ መሻት ሰረጸባቸው። አምላክ መሆንን የሁሉ ገዥ መሆንን ተመኙ። ያን ጊዜም ጥፋትን አጠፉ። ለቅጣትም ከገነት ወጥተው ወደ ምድር ተጣሉ። ይህ ታሪክ ምናልባትም ያለፈ የተረሳና ርባና ቢስ የሆነ አፈታሪክ ሊመስለን ይችላል። በእውነት ቆም ብለን ብናስተውል ግን ታሪክ ብቻ ሳይሆን ዛሬም ላይ እየተካሄደ ያለ ክስተት ነው። የሰው ልጅ በምድር ላይም እየኖረ የቀድሞው ከንቱ ምኞቱ ያ ገዥ የመሆን የበላይ የመሆን ምኞቱ ዛሬም ከልቦናው ውስጥ አልታጣም። ይህ ምኞት ደግሞ ሰውን ለአውሬው ተገዥ ባሪያ ለማድረግ የተጠመደ ወጥመድ ወይም አሽክላ ነው። ዛሬም ህልማችን የበላይ መሆን ነው። ዛሬም ምኞታችን አለቃ መ...
ልጥፎች
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ይድረስ ለአርቲስቶቻችን የትኛው ይቀድማል? እኔ ሁሌም በጣም የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ። እነዚህ አርቲስቶቻችን በየሚዲያው ሲቀርቡ አንድ ደጋግመው የሚናገሩት ነገር አለ። ሁሉም ስለቅጂ መብት ያወራሉ። ህዝቡንም ዋናውን ቅጂ [ኦሪጅናሉን] እንዲገዛ ያሳስባሉ። በዚህም ብቻ አይመለሱም። ማኅበረሰቡ ስለቅጂ መብት ምንም አይነት እውቀት እንደሌለው ደጋግመው ይገልጻሉ። ለመሆኑ ስለየትኛው ሥራቸው ነው የሚያወሩት? ደግሞስ ስለቅጅ መብት መለፍለፍ ነው ወይስ ጥሩ ሥራ ሰርቶ ማቅረብ ነው የሚቀድመው? የትኛው ይቀድማል? እንኳን ኮፒ ተደርጎ በነጻ እንኳን ሊታይ ወይም ሊደመጥ የማይችል ተራ ሥራ እያቀረቡ ስለቅጅ መብት መለፍለፍን ምን ይሉታል? እስኪ የዘመኑን ሙዚቃ እንመልከት። ወይ ግጥሙ አይጣፍጥ፣ ወይ ዜማው አይማርክ ወይ ደግሞ ቪዲዮ ክሊፑ ኢትዮጵያዊ ቃና የለው። ምኑም የማይጣፍጥ ሥራ እያቀረቡ አርቲስት ተብለው ሲጠሩ አለማፈራቸው በጣም ይገርመኛል። ሙሉ በሙሉ ከውጭ ኮርጀው ያመጡና በራሳቸው ፈጥረው እንደሰሩት ሕዝቡን ዋናውን ቅጅ ግዛ እያሉ ሲናገሩ ስሰማ ያናድዱኛል። እነርሱ እየኮረጁ የተኮረጀ አትግዙ ማለት ምን ማለት ይሆን? ማንም እየተነሳ ይጮህና አርቲስት ይባላል። በውኑ የጮኸ ሁሉ አርቲስት ነውን? ምናለ የከበረውን ሙያ ባታረክሱት? ሌላ ስራም እኮ ሞልቷል ሥራ መቀየር ካስፈለጋችሁ። የህዝብን ስሜት መግለጽ ሳይችሉ፣ እንዲሁም ከህዝብ ጎን መቆም ሳይችሉ የህዝብ ልጅ ነኝ፣ ሀብቴም ንብረቴም ሕዝቡ ነው እያሉ ማላዘን ተገቢ አይደለም። ተዋንያንያንን እንመልከት። ገንዘብ ከተከፈላቸው ምንም አይነት ፊልም ከመስራት ወደኋላ አይሉም። ተዋንያኖች ሆይ እስኪ ከመተወናችሁ በፊት የፊልሙን ጭብጥ መርምሩት። ለማህበረሰቡ ያለውን አወንታዊና አሉታዊ ፋይዳ አጥኑት። ...
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ለባርነት የተዘጋጀ ትውልድ >>>>=========<<<< ዓለማችን ከተፈጠረች ጊዜ ጀምሮ አዕላፍት ትውልዶች አልፈዋል። ትውልድ ማለት በአንድ ወቅት ወይም በተመሳሳይ ጊዜ የተወለደና በተመሳሳይ ወቅት የሚኖር የማህበረሰብ ስብስብ ማለት ነው። አባታችን አዳም የመጀመሪያው ሰው እንደሆነ የተለያዩ የሀይማኖት መዛግብት ይናገራሉ። ይሄን ስል ግን አንድ ጥያቄ በአዕምሮዬ መጣ። እውነት ግን ዛሬ በዓለማችን ውስጥ የሚኖሩት ህዝቦች ሁሉ የዘር ግንዳቸው አንድ ነውን? ታዲያ ምን ለያያቸው? በጣም ነው የሚያሳዝነው። ትናንት ከአንድ ዘር ከአንድ አባት ተፈጥረን ዛሬ በየራሳችን ዓለም ውስጥ እየኖርን እኛው ራሳችን ድንበርና ክልል አበጅተን አንዳችን የበላይ ሆነን የራሳችንን ጥቅም ለማስቀደም ስንል ሌላኛውን የበታች አድርገን ለመጨቆን በምናደርገው ትግልና ጥረት ምክንያት እርስበርሳችን አቤልና ቃዬልን ሆነናል። ለዚህም ነው በቋንቋ፣ በቀለም፣ በቦታ፣ በሀይማኖት ተከፋፍለን አጥፊና ጠፊ የሆንነው። ምን ይሆን የሚሻለን? ምን ይሆን ከዚህ ካለንበት የቆሸሸ አካባቢ የሚያወጣን? በዚህ ጽሁፌ እኔ ስላለሁበት ትውልድ (እኔንም ጨምሮ) የታዘብኩትን አንዳንድ ትዝብቴን ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ። ስለዚህ ትዝብቴን ብጥሞና ትታዘቡልኝ ዘንድ እጋብዛለሁ። እኔ በእድሜ የ20ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ እገኛለሁ። ይህ ማለት ደግሞ ሁለት አስርት አመታትን አስተናግጃለሁ ማለት ነው። አቤት እድሜ ግን እንዴት ነው የሚሮጠው? እንደዋዛ እኮ ሃያ አመታትን አሳልፌያለሁ። ወይ ግሩም። የሚገርመው ግን ይሄ አይደለም እነዚህን አመታት ያለምንም ፍሬ ማሳለፌ ነው እንጅ። እናም ወደ ዋናው ጉዳዬ ስመለስ በእነዚህ ባሳላፍኳቸው ሁለት አስርት አመታት ግን እንደአቅሜ ብዙ ነገሮችን ተመልክቻለሁ። ያ...